ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ምክር-አዘል ሃሳቦች
ጥቅምት ፪ሺህ ፪
“ ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ
ኋላ ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ?”
ከገዥው ፓርቲ ጋር ምርጫውን በተመለከተ ምክክር ልበለው ድርድር መያዛችሁ ይሰማል/ይነበባል። መልካም ነው “ ተማክረው…አይሸትም ” ይባል የለ? ግን
አንደኛ፦
አብዛኛዎቻችሁ ገና ከአኹኑ ደጋፊዎቻችሁ እየተጉላሉባችሁ፦ እየተደበደቡባችሁ፦እየታሰሩባችሁ፦ እንዲያውም እየተገደሉባችሁ፦… መኾናቸውን በታላቅ ሃዘን ስትገልጹ ታይታችኋል፦ ተደምጣችኋል፦ ተነብባችኋልም። ይህ ግን ወንጀለኞችን ከነዚህ ዕኩይ ተግባራቸውና
ወንጀሎቻቸው አላገዷቸውም።የድሀ ወገንም ስቃይ አላባራም።
ታዲያ
የነዚህ ሰቆቃዎች ኹሉ ሰለባ የኾኑትና የሚኾኑት፦የማንኛችሁም ደጋፊዎች ቢኾኑ፦ የቆማችሁላቸው የኹላችሁም ወገኖች ኢትዮጵያውያን ናቸው። በተናጠል
ጩኸታችሁ፦ ዋይታቸሁ ፍሬ አልባ ለመኾኑ ማስረጃ የሚገልግ የለም።
ስለዚህ፦
በአንዳችሁ የደረሰው በኹላችሁም እንደደረሰ አድርጋችሁ የኅብረት መፍትሄ መፈለጉ ምን ይመስላችኋል? ለጊዜው የሚታዩኝ፦ለዚህና ዝቅ ስል ለምጨምራቸው አንዳንድ አንኳር-አንኳር የወል ስቃዮቻችሁ በኅብረት ቆማችሁ ልትፈቱት የምትችሉበትን ዘዴ/ዘዴዎች መፍጠሩ ምን ይመስላችኋል?ይህተቀባይነትካገኘለዚህሃሳብአቅራቢ የሚታዩት
፩- በጠቅላይ ሚንስትሩ በአደባባይ እንዲህ ዓይነቶቹ ዕኩይ ተግባራት ብዙ የሚነገርለትን እንዲያውም የሚነበነብበትን ሕገ-መንግሥት የሚጥስ ከባድ
ወንጀል ስለኾነ በቀጥታ እንዲቆሙ በመገናኛ ብዙሃን ኹሉ እንዲታወጅ
መሞከሩ፦
ይህባይደረግበኅብረትሠላማዊሠልፎችን
ሀ- በመላ አገር ላይ እንዲደረግ የኅብረት ጥሪ ብታደርጉ፦
ለ- ውጪ አገር ያሉት ወገኖቻችሁም የፓርቲም ኾነ የቋንቋ ወይም ማንኛውንም
ልዩነታችንን ወደኋላ አድርገን/ጥለን እንደ ቅድመ ቅንጅት በኢትዮጵያዊነት
ለወገን በመቆም ቢቻል ከእናንተ ጋር በአንድ ቀን አልያም በአንድ ሰሞን
ተባበረን እንድንታገል ብትሞክሩ፦
፪- በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ምርጫው እንዲኪያሄድ አንዳንዶቻችሁ ድርድር
መሞከራችሁን ይኽ ጸህፊ በአዎንታ ገጹ ሊያየው ይሞክራል። አፉን ሞልቶ
ለመናገርና ለመቀበል ከዚህ ቀጥሎ የሚቀርቡት አዎንታዊ ሀሳቦች ተቀባይነት
አግኝተው ቢተገበሩ ይረዳዋል። ምርጫ፡ አቻነትን፡ ግልጽነትንና ፍትሃዊነትን ዋልታና ግድግዳ እንደማድረጉ እነዚህን መሠረታዊ ተፈላጊዎችን
ለሟሟላት፡ ከዚህ ቀጥለው የሚቀርቡት ምን ይመስሏችኋል?
ከጠቅላይ ሚንስትሩ እስከ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ወደታችም በየደረጃዎች ወጣቶችንና መምሕራንን እንዲኹም የሃይማኖት መሪዎችን? እየሰበሰቡ በሚቀጥለው ምርጫ ያለፉት ሰቆቃዎች (ቃሉ የኔ ነው) እንዳይደገሙ ሃላፊነት እንዳለባቸው መነገሩ በየመገናኛ ብዙሃን በመደጋገሙ የሚያውቀው ወገን ትንሽ አይኾንም የሚል ግምት አለኝ። ይኽ ዕድል ለተቃዋሚ ፓርቲዎችም መሰጠቱ ከላይ በዋልታና ግድግዳ የመስልኋቸውን ያጠናክራል፤፡ አለመደረጉም የንዚህን መሠረታዊ ተፈላጊዎችን ይንዳል።
ስለዚህ፦
ከላይ ኅብረት እንዲፈጠር ያቀርብሁት ተቀባይነት
አግኝቶ ከኾነ፦
- ዝይህ ዕድል ለተቃዋሚ ፓርቲዎችም እንዲሰጥ ድርድሩ ውስጥ በዓቢይ ደረጃ ቢወሰድ ( ምክንያቱን ሳልዘረዝር)
አፈጻጸሙ ደግሞ በሚከተሉት መንገዶች ቢኾኑ ይጠቅም ይመስለኛል
- ኅብረታችሁ ምርጫውን በተመለከተ ሕግ-መንግሥቱ የሚደነግገውን በተስማማችሁበት የሕግ ምሑር እንዲዘጋጅ ቢደረግ፦
- በዝግጅቱ ከተስማማችሁ በኋላ በየስብሰባዎቹም ይህን አቅራቢ የሕግ ምሑር/ምሑራን ቢኾኑ
- የፓርቲ መሪዎች / ተወካዮቻቸው ለጥያቄ መድረኩ ላይ ተግኝተው በነዚሁ ላይ ብቻ ጥያቄ ቢቀበሉና ቢመልሱ እንጂ
ስለምርጫ ዕቅዳቸው ባያነሱ ለምርጫው “ ሕጋዊነት አቻነትና
ግልጽነት” እንዲኹም በተወዳዳሪዎች መኻክል ( ገዥዎችን
ጨምሮ) ዓይነተኛ መግባባትን ይፈጥራል የሚል ስሜት አለኝ።
፫- ቀጥሎ መለዮ ለባሾች፦
መለዮ ለባሾች ስል ፖሊሶችንም ለዚህ ጽሑፍ መጨመሬ ይታወቅልኝ። በተለመደው አባባል ለአገር ለወገኑ ‘ደሙን የሚያፈስ ስ፡፤…’ ወታደር ወይም ከሕዝብ ጋር በየዕለቱ ብቻ ሳይኾን በየደቂቃው የሚገኘው የፖሊስ ሠራዊት ምርጫው ስለምን እንደኾን ከተወዳዳሪዎች በገዥው ወገን ያለውን ብቻ ይወቅ ማለት ወይ ወታደሩንና ፖሊሱን
- ምንም የማይገባው ደድብ ነው፦ እሰር ሲባል የሚያስር ግረፍ ሲባል የሚገርፍ፦ ዝረፍ ሲባል የሚዘርፍ፦ ተኩስ ሲባል የሚተኩስ፦ ግደል ሲባል የሚገድል ከግዑዝ ከፍ ያለ ከእንስሳ የማይለይ አድርጎ መቁጠር ነው
- አልያም ሕገ-መንግሥታዊ ግዳጁንና መብቱን ካወቀ በዘፈቀደ እንደ ውሻ
“ ቹ !” ስንለው ‘ ለምን? እንዴት?’ እንዳይል ይኾናል።
ስለዚህ፦ መለዮ ለባሹም እንደሰው ተቆጥሮ የምርጫ መብቱንም ዐውቆ እንዲወስን የሚያውቅበትን መንገድ መሻት ይጠቅም ይመስለኛል።
ይህ ኹሉ ነገር የገዥዎችን መግለጫዎች መገናኝያ ብዙሃን እንዳስተጋቡት የተቃዋሚዎችንም ማስተጋባታቸውን ማረጋገጫ ስምምነት መድረሱ ሳይጠቅም ይቀራል?
“ የጨዋ ልጅ ሲጋባ የሚፋታ፦
ሲፋታ የሚጋባ ይመስላል”
ቸር እግዚአብሔር ይጨመርበት።
አሰፋ ስይፉ
ሎንዶን ጥቅምት ፪ ሺህ ፪
ዋና ገጽ