የተቀደሱ ፍልሚያዎችን ድረ-ገጽ ለማስተዋወቅ!
ይህ ድረ-ገጽ:-
የተመሠረተው በዋናነት የምርጫ ፪ሺህን ጉዳይ ለማንሸርሸር ብቻ ነው። ይኽን ስንል ክርክርም ኾነ ሃሳብ ወይም ተቃውሞ ሊንሸረሸር የሚቻለው ስለምርጫው ብቻ ነው ማለት ነው እንጂ ስለአገር ዕለታዊ ጉዳይ አይነበብም ማለት አይደለም። ይህም የተወሰነበት ምክንያት ግልጽ ሊኾን ቢገባውም፦ ለሌላ ሌላ አርዕስት ሰፊ መድረኮች አሉ። እነሱን መሻማት አያስፈልግም። ይበልጥም አንድን ዐቢይ ርዕስ አፍረጥርጦ፡ አብላልቶ፡ አፍታትቶ ለመስማማትም ኾነ ላለመስማማት አንድ መድረክ ላይ ማተኮሩ በብዙ መልኩ ጥቅሙ እየታየ ይመጣል የሚል ዕምነት አለ፤፡ በአኹኑ ጊዜ ደግሞ ቀጣዩን ምርጫ እዚህ ውስጥ መመደቡ ትክክል ይመስላል።
እዚህ ድረ-ገጽ ውስጥ ሃሳባቸውን ለማንሸራሸር የሚሹ ኹሉ
- በገዛ ስማቸው እንጂ በብዕር ስም አይኾንም ( ስማቸውንም የማረጋገጥ መብት ይኖራል። ይህ ሊታለፍ የሚችለው ተሳታፊዎቹ ማንነታቸው ቢገለጽ አገር ወገንን በኅቡዕ ሊረዱ ከሚችሉበት ሥራ የሚደናቀፉ መኾናቸው ሲታመን ብቻ ነው።)
- ማንኛውም ተሳታፊ የኢትዮጵያዊነት ሙሉ ጨዋነት በተሟሉበት ቃላትና አጻጻፍ መኾን አለበት ድረ-ገጹን የሚያስተዳድሩት በተከታይ “ የአዛውንት ያለህ!” በሚለው ጽሑፍ ግልጽ ይደረጋል።
ለማንኛውም ጦርነት ጠላትን ማወቅ፦ ደጋፊዎቹንና ረዳቶቹን መለየት፦ ዐቅሙንና የመረጃዎቹን ርቅቀት (ረቂቅነት) መገምገም ውዘተ አስፈላጊነት የሚያከራክር አይመስልም።
ኢትዮጵያችን ከጦርነት እባሰ አጣብቂኝ ውስጥ መኖርዋ ለአገር ጉዳይ ተከታታዮችና በአገር ጉዳይ ተብከንካኞች አዲስ አይደለም።
ስለዚህ በአባሪነት የቀረበውን በጥሞና አጢነን በዋናነት ልናጠነክረው /ልናሻሽለው እንችላለን። “ በሰላም ጊዜ ብዙ ያላበው( የተዘጋጀ ለማለት ነው)በጦርነት ጊዜ ጥቂት ይደማል!” ነውና!
ማሳሰቢያ
ይህ ድረ ገጽ ኢትዮጵያን ከመከፋፋል ልጆችዋን ከመጨራረስ ለማዳን ለሚታገል በሙሉ በጭብጦቹ ለመወያያ ክፍት ነው።
ዋና ገጽ