ወደ ተቀደሱ ፍልሚያዎች ድረ ገጽ እንኳን ደህና መጡ!    If you can not display Amharic fonts in this site please download Geez fonts here

 

ዋና ገጽ

አላማችን


አንገብጋቢ ፍልሚያዎች

ሊያገኙን ሲፈልጉ

ምርጫ 2002 ላገር ሞት ወይ ሽረት!


ኢትዮጵያችን ምን ዓይነት ኹናቴ ላይ ነች?

(ክፍል ፪)                 
                          
ጥቅምት ፪ሺህ ፪

ጠላቱን ያላወቀ ድልን አይቀምሳትም!

በመጀመሪያው ክፍል ከ፻ ዓመት በላይ ኢትዮጵያን ለመበታተን ሲሸረብባት፦ ሲዶለትባት፦ሲዘመትባት በአባቶቻችን ብልኅነትና ጀግንነት ኃያላኑን ኹሉ መክተው በነጻነት አቆይተዋት ነበር። ለውጪ ጠላት አለመበገሯን ያወቁ ጠላቶቻችን በአገር በቀል ከሃዲዎች ጉድ አደረጉን። በስመ - ኢትዮያዊነት ገብተው የጠላቶችን ዕቅድና ፍላጎት መፈጸም ላይ ናቸው።( የመጀመሪያውን፡ ክፍል ይመልከቱ)     
የትግራይ ነጻ-አውጪዎች ነን ባዮችና ግብረ-አበሮቻቸው ኢትዮጵያን ለመበታተንና ሕዝቧን ሰላም ለመንሳት ከፈጸሟቸው ዕኩይ ተግባራት ውስጥ፡             
                                                   
እስቲ አንዳንዶችን ለአብነት እንጥቀሳቸው፦ብዙዎቻችሁ እንደምታውቋቸው ባውቅም የማያውቁ ሊኖሩ ስለሚችሉ ለዘመቻ ደግሞ ኹሉም ስለሚያስፈልግ፦ ለምታውቁትም ለማስታወሻ እንዲኾን በመመኘት እነሆ!።
ዐበይቱ ላይ ሳተኩር፦

በሽፍትነታቸው ወቅት፦
  • ሻዕብያ ከደርግ ጋር በፌዴሬሽን / ኮንፌዴሬሽን ሊደራደር  ሲፈልግ   ያስቀሩት ሕ.ወ.ሃ. ትግራይ ነበሩ።

  •  ባንኾኮችን ዘረፉ

  • በምጽዋው ጦርነት የመጀመሪያውን ድል ያከሸፈባቸው የባሕር ኃይል ሲኾን በኹለትኛው ዙር ምጽዋን የሚጠብቀውን የታንከኛ ሻለቃ አዛዥ ገዝተው አንድ ጥይት ሳይተኩስ ታንኩን ኹሉ አስረክቦ ባሕር ኃይሉም ሊረዳው በነበረው ታንክ እየተደበደበ በጀግንነት ከተዋጋ በኋላ በ ሕ.ወ.ሃ.ት. ድል
    ኾነ

  • የቀኃሥን ሃውልት ያፈረሰው በዚሁ በተሸጠው የራስ ታንክ ሕ.ወ.ሃ.ት ነበር።

ይኸውም ለትልቁ የባሕር ወደባችንና ለዋናው የባሕር ኃይል መደብ መውደቅ ተጠያቂዎቹ የትግራይ ነጻ አውጪዎች ነን ባዮች መኾናቸውን ያረጋግጣል።

አዲስ አበባ እስከሚገቡ ድረስ አንዳንደዬም ከገቡ በኋላ የሕዝብ  ማመላለሻ አውቶቡሶችንና ትልልቅ የጭነት መኪናዎችን  በምርኮ ስም ከየመጡበት አቅጣጫዎች ዘርፈዋል።            
    

አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ ፦

  • አስቀድመው የገሠገሡት ወደ ብሔራዊና ንግድ ባንኮች፦መከላከያና ቤተመንግሥት  ነበር ከዚያ ወደሌላ-ሌላ ሥፍራዎችም ሄደዋል። ወደቤተመንግሥት የሄዱበትን ጉዳይ ርግጠኛ ስላልኾንኩ  ልተወው። የባንኮቹ ግልጽ ነው። የሚያሳዝነው ግን ከመከላከያና ከሌሎችም ቦታዎች በከባድ-ከባድ የጭነት መኪናዎች ተጭነው ሸራ ለብሰው በውድቅት ወደ ሰሜን መጓዛቸው ነው። የታሪክ ዕቃዎች፡ መለወጫ የማይገኝላቸው ቅርሳ-ቅርሶች ተወስደዋል። ወርቅና የወርቅ ዕቃውም እንዲሁ በወርቅነታቸው ግድ የለም። በቅርስነታቸው ግን ያጎድሉናል። ከዚህ ኹሉ በቶሎ ሊጎዳን የሚችልና ለአደጋ የሚያጋልጠን የአገር መከላከያ የምሥጢር ሰነዶችን ለሱዳን ወስደው ማስረከባቸው ነው። በዓባይ ምክንያት መከላከያችንን አዘጋዝጅተን መኖር ነበረብን። የትግራይ ነጻ-አውጪዎች ነን ባዮች ግን “ታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ”” ሲያውጁ ከተረፈችው ኢትዮጵያ ያለሥጋት ለመኖር

  • ኢትዮጵያን ከውስጥ ርስ-በርሳችንን በክልል በመከፋፈል በየክልሎቹ መኻል ባሉት የማናለብኝና የበዘፈቀደ ድንበሮች ምክንያት በማባላት ነበር፡-

  • ይኽን ሥጋታቸውን በበለጠ ለመቀነስ የመጀመሪያ ተንኮላቸው በብዙ ድካምና ወጪ በረጅም ዘመናት የተዘጋጀውን የመከላከ ሠራዊት መበተናቸው ኢ-ኢትዮጵያዊነታውን ሙሉ በሙሉ   ያረዳበት ኹኔታ  
    ነበር፤፡ የሚረዳ ኖሮ ቢኾን? ወይም አኹንም  ካለ!

  • መንግሥታት በኃይል መለወጣቸው ምንም አዲስ ነገር የለውም። አዲሱ ግን ያለምንም የሠለጥነ ኃይል አገሪቱን ማስቀረታቸው ብቻ ሳይኾን ዘመናዊ ኃይልም ራሳቸው እንዳሉት “ላለመገልበጥ” ፈርተው እንዳይኖር ማድረጋቸው ነው። በአንድ በኩል አገሪቱን ለውጪ ጠላት ማጋለጥ በሌላ በኩል ደግሞ ይኽን ጠላት ሊቋቋም የሚችል ዘመናዊ ኃይል አለማዘጋጀት ጸረ-ኢትዮጵያዊነታቸውን ያጎላዋል።

  • ለመከላከያ ሠራዊት ከሥራ መባረር ብቻ ሳይኾን ጡረታ እንኳን፡ ተክልክለው የ፺፪ቱ ምርጫ ባለቀበት ዕለት ይኽ ጸሐፊ ይፋ ባደረገው “ ትንሳኤ ኢትዮጵያ” በተባለው የመጽሄት መጠን ባለው ጽሑፍ ለወደፊቱ (፺፯ቱ) ምርጫ የሚያገለግሉ መንደርደሪያ አጠቃላይ ዕቅዶችንና ነባሪ ኹኔታዎችን የያዘ ነበር። እዚህ ውስጥ፦

  • ለኤርትራውያን የፖሊስና የመከላከያ ሠራዊቶች ሙሉ የጡረታ   መብታቸውን አክብረው ገዥዎቹ እዚያው ድረስ ሲልኩላቸው
    ለኢትዮጵያውያን ግን ለጡረታ ያዋጡትን አንጡራ ገንዘባቸውን
    እንኳን አንከፍልም ብለው ከባድ አደጋ ላይ እንደጣሏቸ

  • የኢትዮጵያን የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊቶች ሲበትኑ ለኤርትራውያን ግን በጦርነቱ ለተጎዱ ካሳ ለተገደሉባቸው ፈርጠም ያለ ጉማ መክፈላቸውንም አጋልጣለች። ለማንኛውም ጽሑፉ ይፋ በወጣ ፪-፫ ወራት ውስጥ ለኢትዮጵያውያን ሠራዊቶችም ጡረታቸው ተከብሮላቸዋል። ግን ሊሰመርበት የሚገባው መጀመሪያውንስ ኢትዮጵያዊነት ቢኖር እነዚህ ተግባራት እንኳን ሊፈጸሙ ሊታሰብስ ይቻል ነበር

  • ኢትዮጵያዊነት ቢኖር ከ ”ሶሻሊዝም ተላቅቀናል” እያሉ መሬትን ከኢትዮጵያውያን ሊለዩ ይገባ ነበር?

  • ኢትዮጵያዊነት ቢኖር ትግራይ ውስጥ ቤት መልሰው ሌላው አገር ያለውን ከመንግሥቱ ነው የተረክብነው ብለው ይቸበችቡት ነበር?

  • ኢትዮጵያዊነት ቢኖር የማዳበሪያ ንግድ በትግራይ ነጻ-አውጪዎች ነን ባዮች የንግድ ድርጅቶች ብቻ ተይዞ ድሃ ገበሬዎች ገንዘቡን አንችለውም ሲሉ ከመኸር በኋል ትከፍሉናላችሁ እየተባሉ፦ ገበሬዎችም ያን ጊዜም ይወደድብናል ሲሉ “አይወደድም ግድ የለም! እየተባሉ በፍርሃት ከአስገዟቸው በኋላ መኸር ሳይሰበስቡ  ክፈሉ እየተባሉ በራሳቸው ስመ-ዳኞች ሲገደዱ “ ኧረ ስለእግዚአብሔር፦ባይኾን ወቅተን ፤- ከሸጥን በኋላ እንክፈል!” ቢሉም ስመ-ፍርድ ቤቶች ካልከፈላችሁ ታሠሩ እያሏቸው፡ በሬዎቻቸውን እየሸጡ ለከርሞ ማረስ እየተቸገሩ ገበሬዎቹን ከነቤተሰቦቻቸው ለችጋር በዕውቅና በዘዴ የዳረጓቸውን አምላክ ይወቀው ይፍረደው።
  • በእንደዚህ ዓይነት ግፎችና ተንኮሎች ወገን ከእንሣት በታች ተዋርዶ እንዲኖር ተፈልጓል። ተፈርዶበታል፡፡ተደርጓል። ለዚህ ሰቆቃ እኛ ውጪ አገር ያለነው ተባባሪነታችንን እናውቀው ይኾን? በሕግ አንድ ሰው ውሃ ሲወስደው ዋና እየቻለ ሳያድነው ቢቀር በነፍሰ-ገዳይነት እንደሚጠየቅ ኹሉ እኛም ለወገን በብዙ መልኩ ልንደርስለት ስንችልና ሲገባን በየሰበባሰበቡ አልደረስንለትም። ገንዘብ መወወራችንን ክኃልፊነት መዳኛ አርገነው ከኾነ አያዋጣንም።ስለዚህ ተጠያቂዎች ነን። በታሪክ እንጠየቃለን። በነገው ትውልድ እንጠየቃለን። በገዛ ልጆቻችን / የልጅ-ልጆቻችን እንወገዛለን። ያፍሩብናልና! ‘ አገር ወገን እንዲህ ሲኾን ምን አደረግህ/ አደረግሽ ‘ ሲሉ የኾነ ያልኾነውን ብንቀባጥር ያዋጣ ይመስለናል? ወይስ የበለጠ ያዋርደናል?

  • ምን ማለቱ ነው” ተፈልጓል / ተፈርዷል? …” የሚል ካለ የመጀምሪያውን ክፍል እንደገና በጥሞና ያንብብ።ኢትዮጵያን ቀጥቅጦ ለመግዛት ኢትዮጵያውያንን በተለያየ መልክ መከፋፈሉ ብቻ ሳይኾን በስጋውም በአንጎሉም በሥነ ኅሊናውም ማቀጨጭ ስላለባቸው አሳምረው ይዘውታል። ዕድሜ ለትግራይ ነጻ-አውጪዎች ነን ባዮች!

  • በዛሬው ዕለት፦ጥቅምት ፮ ቀን፦ የዓለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ፫ ሚሊዮን ኅፃናት በአስቸኳይ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው ሲናገር በትናንትናው ዕለት ከወገኖቻችን ከ፻ ፵፬ቱ እንደተራቡ እንደሚያድሩ ተዘግቧል። ይኽም ኹናቴ ባለፉት ፳ ዓመታት ውስጥ እየተባባሰ መምጣቱ ተሰምሮበታል።    

  • ይህ ጸሐፊ ለዚህ መፍትሄ ይኾን ዘንድ በፍልሚያ መልክ ወንዞቹ ሞልተው እንዳያጥለቀልቁ / እንዳያጠፉ ደርቀው እንዳይጎዱ ለወገንም ሥራ የሚያሰግኝ፡  በድርቅ ምክንያት አንድም ወገን እንዳይሞት እንስሳም እንዳይበክት እንዲያውም በየጊዜው እየበከተ የሚቀረው እንስሳ የደከመው በውቅቱ ተሸጦ ለባለቤቱ የገቢ ምንጭ እንዲኾንለት ገበያ የማያገኘውም እየታረደ በቀረበው አሳብ መሠረት እሚሠራው መጠለያ ውስጥ ምግብ እንዲኾንለት ከቀረበ በኋላ እጅግ ዓይነተኛ የኾነ ዕድል ተገኘ፡፤ ይኽም ተላላ ጸሐፊ “ እሰየው!” ብሎ ፈነደቀ።ይኽውም በጀርመን ገንዘብ በእሥራኤል ዕውቀት ወንዞችን ለጥቅም ለማዋል ርዳታ መገኘቱ ነበር። ለየትኛው “ክልል”  እንደዋለ መናገር ያሻል?

  • በነገራችን ላይ የውሃ ጉድጓድ መቆፈሪያ ምን ያኽል ችግር እንደኾነ ወገን ያውቀዋል? ለእኛ ዐቅም ማለቴ ነው። አሜሪካን ድምጽ ሬድዮ በዚሁ ክልል ተወላጅ ቃል-አቀባይነት አንድ አካአባቢ ‘ የውሃ ጉድጓዶች በየ ፫ ሜትሮች ተቆፍረው እዚያ ቦታ ላይ ምንም መሥራት አልተቻለም’ ብሏል፡፤ ፍረዱ!

ቀ.ኃ.ሥ.ን ለመውረድ ያበቃቸው ከግማሽ እስከ አንድ ሚሊዮን የሚሊዮን ወገን ለችጋር አደጋ በመጋለጡ ነበር። በደርግ ጊዜ ዓለም በዚያን ዓይነት የተንቀሳቀሰው ፮ ሚሊዮን ወገን ተመሳሳይ አደጋ ላይ በመውደቁ ነበር።

የ.ቀ.ኃ.ሥ ዘመን መሬት በሕዝቡ እጅ ስለነበር ጥቃቱ ከዚያ አላለፈም። በደርግ ጊዜ ግን ሊባባስ የቻለው ሕዝብ መሬቱን ከጠቀማ በኋላ በመኾኑ ነው። ደርግም በአራቱም ማዕዝርን እየተዋጋ እንደነበር ማስታወሱ ይጠቅማል። እነዚህ ግን አገር ዳር-ተዳር ሰላም ነው እያሉ ክ፱-፲፮ ሚሊዮን ወገን ያውም በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በልገሳና በርዳታ እየጎረፈላቸው መራብ መሞቱ የገዥዎቹን ፍጹም ስባዊነትና ምንም ኢትዮጵያዊነት የሌለባቸው መኾኑን አያሳይም?  

በአንጻሩ ለሕዝብ በችጋር ማለቅ ምንም ደንታ የሌላቸው መኾኑን ጌታ በወንጌሉ “ሰውን የማያፍር እግዚአብሔርን የማይፈራ ዳኛ “ እንዳለው መኾኑ አይመስላችሁም?

ሚቀጥለው ፍልምሊያ ለትግራይ ልጆች ስለኾነ እዚያ ላይ የበለጠ የሚባል ይኖራል።

ዓይነ-ኅሊናችንን ከፍቶ ለአገር ለወገን ቋሚዎች ያርገን

ዋና ገጽ